መቅድም

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅደስ አሐደ አምላክ አሜን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በአነደድ ወረዳ
ጥንታዊው የአምበር ቂርቆስ የአብርሃ ወአጽባ ደብረ ቤተክርስቲያን

በቅድሚያ በልዑል እግዚአብሔር ስም የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን በሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተተከለው በግራኝ መሐመድ የተቃጠለው ጥንታዊ አምበር ቂርቆስ ቤተክርስቲያን እርስዎና ሌሎች ምዕመናን በሰጣችሁት ገንዘብ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ገዝተን በማቅረብ የቤተክርስቲያኑን ግንባታ አጠቃላይ የመሰረት ስራውን አጠናቅቀን ከመሰረቱ በላይ ያለውን የግንባታ ስራ በማካሄድ ላይ እንገኛለን።
እስካሁን ላደረጉት በጎ እርዳታ እግዚአብሔር መንግስቱን እንዲያወርስዎ እየጸለይን

አሁንም ቤተክርስቲያኑን አጠናቀን ለመጨረስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለመስራት የሚያስችል አቅም ስለሌለን የተለመደው ትብብርዎ እንዳይለየን በሰማዕቱ በቅዱስ ቂርቆስ ሥም እንጠይቅዎታለን። ስለዚህም እሁድ ነሐሴ 26 ( September 1) ከ4pm – 9pm ሰዓት የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በር/አ/ደ/ሰ/ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተዘጋጅቷል። በዕለቱ ካህናት፤ዘማሪያን፤ መምህራነ ወንጌል እናም ሌሎችም ይሳተፉበታል።


Screen Shot 2013-08-08 at 10.45.17 PM

kirkos.thetewahedo.org
708C01001654 Amber k Kirkos Betekirst Commercial Bank
of Ethiopia Debremarkos Branch
ወይም በቼክ መክፈል የምትፈልጉ ከስር ባለው ሥም ይጠቀሙ
Gedame Tekele Haimanot Bible Association
አድራሻ P.O.Box 13354, silver spring MD, 20911
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 202- 390- 6599
0911027701 0913184330